«ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም» በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ የፓናል ዉይይት ተካሄደ፡፡
👉17ተኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የፓናል ውይይት አካሂዷል ::
👉በፓናል ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተገኝተው ለህዝቡ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
👉የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ፣ የአዲስ አበባ የመንግስት በጀት ወጭ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጋቶዌች ዎር፣አቶ ብስራት ማጆሬ የየካ ክ/ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና የክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባላቶች ተገኝተዋል፡፡
👉በፓናል ውይይቱም ኢትዮጵያ ዊ እሴቶች ፣ ባህሎችን ይዞን ዲምክራሲያዊ አንድነታችን በማጠናከር ዘላቂ ሰላም ፣ልማትና እድገት እንዲኖር ትኩረት ተደረጎ ይሰራል ተብሏል፡፡
👉አቶ ጋቶዌች ዎር የአዲስ አበባ የመንግስት በጀት ወጭ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ብሄሮች ፣ብሄርሰቦችና ህዝቦች የሉዓላዊነታቸው መግለጫ የሆነውን ሕገ መንግስት ቀጣይነት ላለው ልማት ፣ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መጠናከርና ለህገ የበላይነት ለማረጋገጥ ንቃተ ህገ መንግስትን ማጎልበት የማይተካ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
👉ተወያዮቹ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን መንግስት እየሄደበት ያለውን ሂደት አድንቀው፤ ችግሮችን በንግግርና በምክክር ለመፍታት የሄደበት ርቀት የሚደገፍ መሆኑን ገልፀዋል፡
👉የተጀመረውን የሰላም ሂደት ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቅንነትና በኃላፊነት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡





